ሀገሬ ቲቪ

ብቅል ፋብሪካ በኢትዮጵያ

በ60 ሚሊዮን ዩሮ የተገነባው ሱፍሌት ማልት ብቅል አምራች ፋብሪካ ተመረቀ፡፡

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ፋብሪካው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በግብርና ላይ የሚሰራ ኢንቪቮ ግሩፕ በተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ሥር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች፤ 90 የኢንዱስትሪ መንደሮች እና 13 ሺሕ ሠራተኞች አሉት፡፡

በኢትዮጵያ ያሉት ኹሉም የቢራ ፋብሪካዎች በዓመት 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሔክቶ ሊትር ነው፤ ለዚህ የሚያስፈልገው ደግሞ 117 ሺሕ 600 ቶን ብቅል ነው፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-13