
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች ለሰብአዊ ቀውስ ተጋለጡ።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኤም 23 የተሰኘው ታጣቂ ቡድን ከሀገሪቱ ሠራዊት ጋር ጦርነት ውስጥ መግባቱ ዜጎችን ለሰብአዊ ቀውስ መዳረጉ ተገልጿል።
በሀገሪቱ ከባድ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ዜጎች ከቤታቸው እና ሰፈራቸው እየተፈናቀሉ መኾኑን አልጀዚራ ዘግቧል።
ውጊያው እየተካሔደበት በሚገኘው ጎማ ተብላ በምትጠራው ግዛት ውስጥ ያሉ ዜጎች ከመሰደድ ባለፈ ለምግብ ዕጥረት ተጋልጠዋል።
በማህሌት አማረ
2024-02-27