ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በዝቋላ ገዳም የደረሰውን ጥቃት አወገዘ።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በዝቋላ ገዳም የደረሰውን ጥቃት አወገዘ።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ሸዋ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዝቋላ ገዳም ባለፈው ሳምንት በአራት መነኮሳት ላይ የተፈጸመውን ግድያ ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

ጉባዔው መንግሥት በመነኮሳቱ ላይ የተፈጸመውን የግፍ ግድያ አጣርቶ ተጠያቂዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብና በስጋት ቀጠና ውስጥ ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎች የኃይማኖት ተቋማት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቋል።

የኃይማኖቶች ጉባዔው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃይማኖት ተቋማትና አባቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ ኢ-ሰብዓዊ አያያዞችና መዋቅራዊ በደሎች ሕጋዊ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ኢ-ፍትሃዊ ተግባራት እንደኾኑም ገልጧል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-02-27