የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በግማሽ ዓመቱ 3 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
ተቋሙ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከሚሰጡ አገልግሎቶችና ከሌሎች የገቢ ምንጮች 23 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም ተናግሯል።
በግማሽ ዓመቱ የድርጅቱን መርከቦችና የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም ከ1 ሚሊዮን ቶን በላይ ዕቃ ለማጓጓዝ ታቅዶ ከ2 ሚሊዮን ቶን በላይ ማጓጓዝ መቻሉን ከማህበራዊ ትስስር ገፁ ተመልክተናል።
ተቋሙ በወጪ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ለምርት ግብዓትነት ለሚያስገቧቸው ጥሬ ዕቃዎች፣ ከየብስ ትራንስፖርት የትርፍ ህዳግ እንዲሁም ከባህር ትራንስፖርት የትርፍ ህዳግ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-28
