
የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀን በተባበሩት መንግስታት እውቅና የተሰጣትን ምዕራብ ሊቢያን ጎብኝተዋል።
አልቡርሃን በሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት መሀመድ ዩኑስ አል መንፊ በሱዳን ጦርነቱ በተጀመረ ሰሞን የተደረገውን ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት አወድሰዋል።
ሁለቱም ተፋላሚዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ፍላጎት እንዳላቸውም ፕሬዝዳንቱ ጨምረው አስታውቀዋል።
በሱዳን ላለፉት 10 ወራት እየተደረገ ባለው ጦርነት ከ12, ሺ በላይ ሱዳናውያን ህይወታቸውን ተነጥቀዋል።
በናርዶስ ታምራት
2024-02-28