በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጅዎችን ለማፅዳት እና ለማምከን የ1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተደረገ።
በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ለማፅዳት እና ለማምከን የሚውል የአንድ ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ።
ይህን ድጋፋ ዴንማርክ ማድረጓን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፈንጂ ማፅዳት ተግባር አገልግሎት አስታወቀ።
ድጋፉ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን ለሚደረገው የፈንጅ ማፅዳት ተግባር የሚል ነው ተብሏል።
በትግራይና በአፋር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ የተቀበሩ ፈንጅዎችና የመሳሪያ ቅሪቶች የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ እንደሚረዳ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፈንጂ ማፅዳት አገልግሎት በመካነ ድሩ አስፍሯል።
የፈንጂ አፅጂ ቡድኑ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ትክክለኛ መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ እንዲሁም ቴክኒካል ምርመራዎችን ማድረግ መጀመራቸውም ተመላክቷል።
በሳምሶን ገድሉ
2024-02-28
