ሀገሬ ቲቪ

ኦቻ ለኢትዮጵያ 17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቀ

ኦቻ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ችግርን ለመቅረፍ 17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ኦቻ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ነው ያሉትን የምግብ ዋስትና ችግርን ለመቅረፍ 17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቀ።

የቢሮው የአደጋ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝ ገንዘቡ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ጉዳት እየደረሰባቸው ለሚገኙ ለአፋር፣ አማራ እና ትግራይ አካባቢዎች የሚውል ነው ብለዋል።

ድርቁ እየተባባሰ በመምጣቱ በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ ፈላጊ እንደሆኑ ይገመታል ሲል ቢሮው በመካነ ድሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በፂዮን ታደሰ
2024-02-28