ሀገሬ ቲቪ

በአማራ፣ በትግራይ እና አፋር ክልል በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

በአማራ፣ በትግራይ እና አፋር ክልል በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ኃይል የተቋረጠው ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ ኃይል መቋረጡ ተሰምቷል።

ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፍድ ጀምሮ በንፋስ መውጫ አካባቢ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ አንደኛው ፌዝ በመበጠሱ የተነሳ ከንፋስ መስጫ - ጋሸና- አላማጣ - መሆኒ - መቀሌ የሚሄደው መስመር ኃይል መቋረጡ ተነግሯል።

በተመሳሳይ ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ ከተሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችም ኃይል መቋረጡን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

ከኮምቦልቻ በባቲ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር ክልል መዲና ሰመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።

በናርዶስ ታምራት
2024-03-05