የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል 3 ሺሕ ቶን ምግብ ማከፋፈሉን አሳወቀ፡፡
ተቋሙ ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች መላኩ ይታወሳል፡፡
አሁንም እርዳታ የጫኑ 94 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያቀኑ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በአፋር እና በአማራ ክልልም የምግብ እርዳታ ለማሰራጨት በሂደት ላይ ነው፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-13
