ሀገሬ ቲቪ

ፐርፐዝ ብላክ ከቢጂአይ-ኢትዮጵያ ጋር የገባሁትን የመሬት ሽያጭ ስምምነት በውል እና ማስረጃ በኩል ለማሰር ዝግጁ ነኝ አለ፡፡

ፐርፐዝ ብላክ ከቢጂአይ-ኢትዮጵያ ጋር የገባሁትን የመሬት ሽያጭ ስምምነት በውል እና ማስረጃ በኩል ለማሰር ዝግጁ ነኝ አለ፡፡

ሜክሲኮ የሚገኘዉን የቢጂአይ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ዙሪያ በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ የተባሉት ተቋማት መካከል ስምምነት ተደርሶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ቢጂአይ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙኃን ባሰራጨው መረጃ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ መገደዱን ጠቁሟል፡፡

ይህንኑ በተመለከት ፐርፐዝ ብላክ በሥራ ኃላፊዎቹ በኩል ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ከቢጂአይ-ኢትዮጵያ የገባውን ስምምነት ተፈፃሚ ያልሆነው ቢጂአይ ኢትዮጵያ በውል እና ማስረጃ በኩል ለመዋዋል ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነዉ ሲል ወቅሷል፡፡

ተቋሙ በውል እና ማስረጃ ስምምነቱን ለመጨረስ ፍላጎት ካለው የሁለተኛ ዙር የክፍያ ሂደት ለመፈፀም ቁርጠኛ ነኝ ብሏል።

ሀገሬ ቴሌቪዥን በጉዳዩ ላይ ከቢጂአይ-ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃ ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡

በይስሃቅ አበበ
2024-03-05