ኢቲ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል።
ፋብሪካው በሰዓት 150 ቶን፣ በቀን 3 ሺህ 600 ቶን የታጠበ ከሰል የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡
ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የታጠበ ከሰል ፍላጎትን 75 በመቶ የመሸፈን አቅም አለው ተብሏል።
በፋብሪካው የሚሠሩ ቋሚ ሠራተኞች ሥልጠና ወስደው የሙከራ ሥራዎች የተጀመሩ ሲሆን በቅርቡ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር መነገሩን ፕረስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በቂ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ያላት ቢሆንም የድንጋይ ማጣሪያ ፋብሪካ ባለመኖሩ በውጭ ምንዛሪ ገዝታ የታጠበ ከሰል እንደምታስገባ ይታወቃል፡፡
በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-05
