ሀገሬ ቲቪ

ቻይና የመከላከያ በጀቷን በ7.2 በመቶ ማሳደጓን አስታወቀች።

ቻይና የመከላከያ በጀቷን በ7.2 በመቶ ማሳደጓን አስታወቀች።

ቻይና ለመከላከያዋ የምትመድበዉን በጀት በ7.2 በመቶ ማሳደጓን፤ ዛሬ በተጀመረዉ የህግ አዉጪዎች አመታዊ ጉባኤ ላይ አስታዉቃለች።

በዚህም 1.6 ትሪሊዮን ዩዋን ወይም 222 ቢሊዮን ዶላር ለመከላከያ ሀይል በጀት በመበጀት ከአሜሪካ ቀጥሎ ይዛዉ ይነበረዉን የሁለተኝነት ደረጃ፤ በዚህም ዓመት ይዛ እንደምትቀጥል ቲአርቲ ዘግቧል።

በህግ አዉጪ ጉባኤዉ ላይ፤ በያዝነዉ የፈረንጆቹ 2024 ዓመት የቻይና ዕድገት 5 በመቶ ሊሆን እንደሚችል የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-03-05