ሀገሬ ቲቪ

በሰሜናዊ ጋዛ ሕፃናት በረሃብ ሳቢያ እየሞቱ ነው ተባለ

በሰሜናዊ ጋዛ ሕፃናት በረሃብ ሳቢያ እየሞቱ ነው ሲሉ የዓለም የጤና ሚንስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ተናገሩ።

በጋዛ ቢያንስ 10 ሕፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት መሞታቸውን አረጋግጠናል ብለዋል ኃላፊው።

ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች በሰሜናዊ ጋዛ ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለ ያነሱት ኃላፊው የምግብ እና የህክምና መድሃኒት እና ቁሳቁስ እጥረት ከሆስፒታሎች መፍረስ ጋር ተደምሮ ጋዛን ሰዎች ከሞት የማያመልጡበት አድርጎታል ብለዋል።

በእስራዔል እና ሀማስ መካከል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከ30,500 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለውል።

በናርዶስ ታምራት
2024-03-05