በቀጣዮቹ ሳምንታት ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ይደርሳል ተባለ።
በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርስ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
አሁን ላይ ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ 510 ሺህ ኩንታል ዩሪያ የጫነች 'አባይ ሁለት' መርከብ ጂቡቲ መድረሷንም ተናግሯል።
እስከ አሁን ከ9 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ወደብ መድረሱን ኮርፖሬሽኑ ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ውስጥም 8 ሚሊየን 731 ሺህ 403 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑም በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል፡፡
በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-06
