ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20 ቦይንግ 777X-9 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የቦይንግ ከፍተኛ የንግድ እና ማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ብራድ ማክሙለር ተፈራርመዋል።

አውሮፕላኑ 65 ቶን የመሸከም አቅም እንዳለው የተነገረ ሲሆን 71 ሜትር ርዝመት ያለው የአውሮፕላኑ ክንፍ መታጠፍ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡

በስምምነቱ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2027 ጀምሮ እስከ 2030 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 8 አውሮፕላኖችን ለመረከብ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ የገዛቸው አውሮፕላኖች 104 መድረሳቸው ተመላክቷል ሲል አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-06