ሀገሬ ቲቪ

በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም የሚደረግበት እድል ስለመኖሩ አሜሪካ ተናገረች።

በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም የሚደረግበት ዕድል ስለመኖሩ የአሜሪካዉ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ተናገሩ።

ብሊንከን ከኳታሩ አቻቸዉ ሼክ ሞሐመድ ቢን አብዱራህማን አል ታኒ ጋር በመከሩበት ወቅት፤ በጋዛ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ ተኩስ አቁም ሊደረግ የሚችልበት ዕድል ስለመኖሩ መናገራቸዉን አናዶሉ ዘግቧል።

በተኩስ አቁሙ ሐማስ ያገታቸዉን እስራኤላዊያን እንዲለቅ እና ለፍልስጤማዊያን የሚደርሰዉ ሰብዓዊ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር የሚያደርግ ነዉ ብለዋል።

በእስራኤል እና ሐማስ መካከል ለሚካሄደዉ ንግግር፤ የአሜሪካ፣ የኳታር እና የግብፅ ድርሻ የጎላ እንደሆነ ተነግሯል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-03-06