ቡና አቅራቢዎች ቡናቸውን ለላኪዎች ሲያቀርቡ ክፍያ በትክክለኛው መንገድ ስለማይከወንላቸው ከገበያ ለመውጣት መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
አቅራቢዎቹ ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ከአርሶ አደሮችና ከቡና አቅራቢዎች ጋር ውይይት ባካሄደበት መድረክ ላይ ነው።
አብዛኛዎቹ ቡና አቅራቢዎች ንብረታቸውን አስይዘው ከአርሶ አደሩ ቡና ከገዙ በኋላ ለቡና ላኪዎች በሚሸጡበት ጊዜ፣ ላኪዎቹ ‹‹የሸጣችሁልን ቡና የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ያስቀመጠውን መሥፈርት አላሟላም›› በማለት ዓመቱ ሙሉ ገንዘባቸውን ይዞ እንደሚያንገላቷቸው በመድረኩ አንስተዋል።
መንግሥት ብዙ ጊዜ ለላኪዎች ብቻ ትረኩት በመስጠቱ ሳቢያ ከባንክ በአግባቡ ብድር ባለማግኘታቸው ቡናቸውን በኪሳራ ለመሸጥ መገደዳቸውን አቅራቢዎች መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-11
