ሀገሬ ቲቪ

ጊዜ ያለፈባቸው 1.5 ሚሊዮን መተግበሪያዎች

አንድ ሦስተኛው የአፕል እና የጎግል መተግበሪያዎች ጊዜ ያለፈባቸው ናቸው ተባሉ፡፡ አዲስ ይፋ የሆነው ጥናት እንዳመላከተው በጎግል እና አፕል የመተግበሪያ ማከማቻዎች ላይ 1.5 ሚሊዮን አፕሊኬሽኖች በሁለት ዓመታት ውስጥ ያልተሻሻሉ በመሆናቸው እክል ሊገጥማቸው ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡

ጎግል ከሁለት ዓመት በላይ ጥቅም ላይ ያልዋሉ 869ሺሕ ገደማ መተግበሪያዎች ሲኖሩት አፕል ደግሞ 650ሺሕ አካባቢ አለው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ይመስላል አፕል እና ጎግል በመተግበሪያ አበልጻጊዎቻቸው ችላ የተባሉ መተግበሪያዎች ላይ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል አዲስ ፖሊሲዎችን ያሳወቁት፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ማሻሻያ የተደረገባቸው መተግበሪያዎች በበርካታ ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ ዳውን ሎድ የተደረጉ ናቸው ሲል ሲኔት ጽፏል::

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-13