ሀገሬ ቲቪ

በደቡብ አፍሪካ ለሚደረገዉ ምርጫ ለመሳተፍ 115 ፓርቲዎች ጥያቄ አቀረቡ

በግንቦት ወር በደቡብ አፍሪካ በሚደረገዉ የፓርላማ ምርጫ ላይ ለመወዳደር 115 ፓርቲዎች ጥያቄ ማቅረባቸዉን የሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀዉ፤ 115ቱ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ፓርላማ መቀመጫ ለማግኘት በሚደረገዉ ዉድድር ዉስጥ ለመሳተፍ ጥያቄ አቅርበዋል።

ከእነዚህ ዉስጥ፤ 14 የሚሆኑት ፓርቲዎች አሁንም በፓርላማ መቀመጫ ያላቸዉ ናቸዉ የተባለ ሲሆን፤ 101 የሚሆኑት ደግሞ በሀገሪቱ ፓርላማ ዉስጥ ምንም መቀመጫ የሌላቸዉ መሆናቸው ተነግሯል።

ኮሚሽኑ በፓርቲዎቹ የቀረበዉን የዉድድር ጥያቄ እንደሚመረምር እና ብቁ ሳይሆኑ የተገኙትን ከዉድድሩ እንደሚያሰናብት ተገልጿል።

በበላይሁን ፍስሐ
2024-03-11