የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የሩሲያ ጦር ወደ አውሮፓ ሀገራት እንዲዘምት አልፈቅድም ማለታቸውን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል።
የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬናዊያንን በመደገፋቸው የሩሲያ ጦር ልታዘምትባቸው አትችልም ሲሉ በምስል ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል።
ሩሲያ በፈረንጆቹ 2020 በየካቲት ወር በከፈተችው ጥቃት የተጀመረው ጦርነት ላይ ዩክሬናዊያን ለሀገራቸው እየተከላከሉ ነው ብለዋል።
የሩሲያን የአየር ኃይል ማጥፋት የሚችል አየር ኃይል እየገነቡ መሆናቸውን ዘለንስኪ ጠቁመዋል።
የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት ከኹለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ረጅም ቀናትን የፈጀ የመጀመሪያው ጦርነት እንደሆነም ተነግሯል።
በማህሌት አማረ
2024-03-11
