ሀገሬ ቲቪ

ደቡብ ኮሪያ ወታደሮቿን ወደ ሆስፒታሎች ልታሰማራ ነው

ደቡብ ኮሪያ 20 ወታደር የቀዶ ሕክምና ሀኪሞችን እና 138 ወታደር ጠቅላላ ሀኪሞችን ወደ 20 ሆስፒታሎች እንደምታዘምት አስታወቀች።

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ሊያደርገው ያሰበውን የህክምና ማሻሻያ ዕቅድ ተከትሎ በ100 ሆስፒታሎች እያገለገሉ የነበሩ 12 ሺ ሰልጣኝ ሀኪሞች የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትር በሕክምና ተቋማት እንዲያገለግሉ ግዳጅ የተጠሩት ወታደር ሀኪሞች ደቡብ ኮሪያ ካላት ከ2,400 ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው ማለታቸውን አልጄዚራ አስነብቧል።

ሰልጣኝ ሀኪሞቹ አድማ በማድረጋቸው ሳቢያ ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት አጥተዋል፤ የሀገሪቱም የጤና ሥርዓት ተዛብቷል ሲል ዘገባው ጨምሮ አትቷል።

በሳምሶን ገድሉ
2024-03-11