ሀገሬ ቲቪ

የሱዳን ጦር ለረመዳን ፆም ተኩስ እንደማያቆም ተናገረ

የሱዳን ጦር ለረመዳን ጾም ተኩስ እንደማያቆም ገለጸ፡፡

በሱዳን ጦር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል በትናንትናው እለት የተለቀቀው የአታ መግለጫ እንደገለጸው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በባለፈው ግንቦት ወር በሳኡዲ አረቢያ እና በአሜሪካ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ጦራቸውን ከሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ የማያስወጡ ከሆነ የረመዳን ተኩስ አቁም አይኖርም ብለዋል፡፡

በጄነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር ግን በተመድ የቀረበውን የተኩስ አቁም ጥሪ መቀበሉን ገልጿል።

በናርዶስ ታምራት
2024-03-11