ሀገሬ ቲቪ

የግብርና ሚኒስትር ከዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ፍሎሪበርት ንጋሩኮ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ፡፡

በዓለም ባንክ የበጀት ድጋፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመተግበር ላይ መሆናቸውን ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገልፀው፤ ባንኩ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ይበልጥ እንዲያግዝ ጠይቀዋል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የኤክስፖርት ምርትን በስፋት እና በጥራት ለማምረት እንዲሁም ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ባንኩ እንደሚደግፍ መናገራቸውን የግብርና ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።

በናርዶስ ታምራት
2024-03-11