የ114 ተፈታኞች ውጤት ተሰረዘ።
በመውጫ ፈተና ኩረጃና ሌሎች የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የተማሪዎች ውጤት የተሰረዘው ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት፣ መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት በመፈፀማቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ ለሁሉም የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል፡፡
በነዚህ ተፈታኞች ላይ የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገልፅ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
የከፍተኛ ተቋማት የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።
በብሩክታዊት አሥራት
0000-00-00
