ሀገሬ ቲቪ

ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ መርምሮ አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ16ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበለትን የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ደንብን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል፡፡

ደንቡ ባለስልጣኑ ልዩ ችሎታ ያላቸውን ሰራተኞች ለመቅጠርና ለማቆየት እንደሚያስችለውም ተጠቁሟል፡፡ ደንቡ ባለሥልጣኑ ነፃና ገለልተኛ ተቋም መሆኑን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መዘጋጀቱን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አስገንዝበዋል።

በደንቡ ዝግጅት ወቅት የህግ ባለሙያዎች፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የሚዲያ አካላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት የአስረጂዎች ውይይት መካሄዱን ከምክር ቤቱ ማህበራዊ ገፅ ተመልክተናል።

በናርዶስ ታምራት
2024-03-12