ሀገሬ ቲቪ

የሕዳሴው ግድብ ገቢ መጨመር

ባለፉት አራት ወራት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ338 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ። ከሐምሌ1 እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ገንዘቡ ሊሰበሰብ የቻለው። እስከ ጥቅምት 30/2014 ዓ.ም ድረስ 338 ሚሊዮን 588 ሺሕ 367 ብር ሰብሴያለው ሲል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። በ2013 ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን በሃምሌ እና ነሐሴ ወር ብቻ 201 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል። ይህም ህብረተሰቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ማሳያ እንደሆነም ነው የተነገረው። በተያዘው ዓመትም 2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ሰምተናል። የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 2014 ድረስ ከ16 ቢሊዮን 67 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል። ግድቡ በቅርቡ 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ተብሎም ይጠበቃል። የግድቡ ኝባታ አሁን ላይ 82 በመቶ መድረሱን ከሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-08