ሀገሬ ቲቪ

የ100 ቢሊዮን ብር ልዩነትያለው በጀት

መንግሥት ለቀጣዩ ዓመት 780 ቢሊዮን ብር በጀት ሊይዝ ነው ተባለ፡፡ ከሁለት ወር በኋላ ለሚጀምረው አዲሱ የበጀት ዓመት ካለፈው ዓመትጋር ሲነፃፀር የአንድ መቶ ቢሊዮን ብር ያህል ብልጫ አለው፡፡

የ 2014 ዓ.ም በጀት የአጋማሽ ዓመቱ ጭማሬ ተዳምሮ 680 ቢሊዮን ብር እንደነበር አይዘነጋም፡፡ መንግሥት አሁን ያሰናዳው 780 ቢሊየን ብር በጀት ከፍ ያለ ጉድለት ሊገጥመው እንደሚችል በተደረጉ ምክክሮች ላይ መነሳቱን ሰምተናል ሲል ዋዜማ ዘግቧል፡፡

ለ2015 ዓ.ም የተያዘው በጀት ከ2014 ጭማሬ ቢኖረውም በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሲሰላ ብዙም ለውጥ የለውም ተብሏል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-13