ሀገሬ ቲቪ

በሱዳን 230 ሺህ ሕፃናት እና አራስ እናቶች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ

በሱዳን 230 ሺህ ሕፃናት እና አራስ እናቶች ለረሃብ ስጋት መጋለጣቸውን ሲል አንድ አለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታውቋል።

ድርጅቱ ወሳኝ እርምጃ የሚወሰድ ካልሆነም ዜጎቹ በረሃብ ሊሞቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

ድርጅቱ "በሱዳን ከ2 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ህጻናት እና ተጨማሪ 729,000 ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በከፋ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነው" ሲል ተናግሯል።

በሁለት ተቀናቃኝ ጄኔራሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት 11 ወራትን ሲያስቆጥር፤ ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድል ስምንት ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ማስታወቁን ቲአርቲ ዎርልድ ዘግቧል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-13