በዘንድሮ ዓመት 265 የኖራ ማዘጋጃ ፋብሪካዎች እየተገነቡ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ለነዚህም 944 ሚሊየን ብር እንደተመደበ ተነግሯል።
በኦሮሚያ ክልል የአፈር አሲዳማነትን ሙሉ ለሙሉ ለመከላከል ከ57 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ኖራ እንደሚያስፈልግም የክልሉ ግብርና ቢሮ ጠቁሟል።
የጉደር ኖራ ማዘጋጃ ፋብሪካ በቀን እስከ 3 ሺህ ኩንታል ኖራ እንዲያመርት መደረጉን እና እስካሁን ከ141 ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ ማምረቱ ተነግሯል።
በበጀት ዓመቱ መጨረሻም እስከ 300 ሺህ ለማምረት ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ ተጠቁመዋል።
በማህሌት አማረ
2024-03-16
