ሀገሬ ቲቪ

ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያሰመዘገበው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

ኩባንያው ይህን ያስታወቀው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

በፓርኩ ለባለሀብቶች የሚቀርቡ እንደመብራት፤ ውሀ እና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶች ክፍያ ከሌሎች ተመሳሳይ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑንና ይህም ለኢንቨስትመንት ውሳኔያቸው ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ኩባንያው ገልጿል።

ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ እ.አ.አ በ2011 የተቋቋመና ተቀማጭነቱን በቻይና ያደረገ ኩባንያ ሲሆን በሳውዲ አረቢያ፤ በጋና፤ በናይጄሪያ፤ በኢራን እንዲሁም በአዘርባጃን የፋይበር፤ በሴራሚክ፤ በአልሙኒየምና በሌሎች የምርት አይነቶች ተሰማርቶ የሚገኝ ግዙፍ ኩባንያ መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-26