በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት "የአልነጃሺ መስጂድ" እስካሁን ድረስ አለመጠገኑ ተገለፀ።
በትግራይ ክልል ከውቅሮ ከተማ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ጥንታዊው "የአልነጃሺ መስጂድ" በኅዳር ወር 2013 ዓ.ም በክልሉ በነበረው ጦርነት ነበር ጉዳት የደረሰበት።
እስካሁን ድረስ መስጅዱ ምንም ዓይነት ጥገና እንዳልተደረገለት፤ የመስጂዱ ኢማም "ሼህ አደም መሐመድ ኢብራሒም" ለጣቢያችን ተናግረዋል።
"አደጋው ከደረሰ በኋላ የፌደራል እና የተለያዩ ተቋማት መስጂዱን አይተው፤ ለጥገና ቀይሰው ነበር፤ ነገር ግን በተግባር ያየነው ነገር የለም" ሲሉ ሼህ አደም ገልፀዋል።
ይህ ትልቅ ታሪክ ያለው የሀገር ቅርስ በጦርነት የደረሰበት ጉዳት በአግባቡ ሳይጠገን አራተኛ ዓመቱን ሊይዝ ነው ሲሉ ሼሁ ተናግረዋል።
በአፍሪካ የመጀመሪያው መስጂድ የኾነው አልነጃሺ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ "ሁለተኛው መካ" ተብሎ ይጠራል።
በ ሙሉጌታ በላይ
2024-03-26
