ሀገሬ ቲቪ

ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እየተከናወነ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላና አካባቢው ያሉ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ በ172 ሚሊየን ብር ወጪ የመስመር ዝርጋታ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰታወቀ።

መስመሩ ዝርጋታው ከኮዬ-አቦ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ቦሌ ቡልቡላ የሚደርስ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል።

አሁን ላይ ያሉ ደንበኞችን በቂ የኃይል እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ፤ በአካባቢው በርካታ የቤቶች ግንባታ የሚከናወንበት በመሆኑ በቀጣይ የሚኖረውን የኃይል ፍላጎት ለማስተናገድም ያስችላል ተብሏል፡፡

አሁን ላይ አጠቃላይ የሲቪል ስራዉ አፈፃፀም 80 ፐርሰንት የደረሰው ይህ ፕሮጀክት፤ ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና ግንባታው ለሀገር በቀል ኩባንያዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማህበራዊ ገፅ ተመልክተናል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-26