ሀገሬ ቲቪ

አንጋፋዋ አርቲስት እናኑ ደጉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

አንጋፋዋ አርቲስት እናኑ ደጉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በባህል ቡድን ውስጥ ለረጅም ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ሀገሯን በከፍተኛ ቅንነትና ንቃት ስታገለልግል የቆየችው በተለይም በፉከራ፣ ሽለላ እና ቀረርቶ ሥራዎችዋ በህዝብ ዘንድ የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት እናኑ ደጉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

የአንጋፋዋ አርቲስት እናኑ ደጉ የቀብር ሥነ_ስርዓት ዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 በሰሚት ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡

ሀገሬ ቴቪ ለቤተሰቦችዋ፣ ለባልደረቦችዋ፣ ለወዳጅ ዘመዶችዋ እና ለአድናቂዎችዋ መፅናናት ይመኛል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-30