ሀገሬ ቲቪ

የሴኔጋሉ አዲሱ ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ጦር አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ሊጠይቁ ነው።

የሴኔጋሉ አዲሱ ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ጦር አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ሊጠይቁ ነው።

የሴኔጋል የህገ መንግስት ምክር ቤት የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ባሲሮ ዲዮማዬ ፈዬ ፕሬዝዳታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይታወቃል።

ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ያሸነፉት 54 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው።

የስልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀውን ፕሬዝደንት ማኪ ሳልን የሚተኩት ፈዬ በመጭው ሚያዝያ ሁለት ቃለ መሃላ ይፈጽሟሉ ተብሏል።

ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በፈረንጆቹ የካቲት 25 እንዲካሄድ ቀነ ገደብ ተቆርጦለት የነበረውን ምርጫ በማራዘማቻው በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-30