የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
ከዚህ ቀደም ባንኩ ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ ጥሪ ባደረገው መሰረት ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው ክፍያ የጨረሱ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 10 ሺህ 857 ከፍ ማለቱን ተናግሯል።
የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ያልጀመሩ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 222 ዝቅ ያለ ሲሆን ከእነዚህ ግለሰቦች የሚጠበቅ ገንዘብም ወደ አራት ሚሊየን ብር መሆኑን ባንኩ ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ብልሽት ምክንያት ከ801 ሚሊየን ብር በላይ ተወስዶበት እንደነበር ማስታወቁ ይታወሳል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-04-01
