አበባ ተስፋዬ ከተወሰኑ ወራት በፊት በብሄራዊ ቲያትር አከባቢ ልጇን ይዛ የእለት ጉርሷን ለማግኘት የሰዎች አይን ይገርፋ እንደነበር አጫውታናለች።
“ትምህርት ቤት ጎደኛ ነበረኝ በአጋጣሚ አረገዝኩና ቤተሰቦቼ እንዳያዩኝ በሚል ከጠፋሁ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ አንድ ቀን ምርር ብሎኝ ሳለቅስ አይቶ አንድ ግለሰብ ነው ወደዚህ ድርጅት ከነ ልጄ ያመጣኝ።”
22 ዓመታትን ተስፋ ለሌላቸው ህጻናት ተስፋ በመሆን የዘለቀው ተስፋ ለህጻናት ድርጅት ሰብአዊ አገልግሎት ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ወጣቶችና ልጅ ያቀፉ ህጻናትን የመደገፍ እና በዘላቂነት የማቋቋም ፕሮግራም ጀምሯል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በመጀመሪያ ዙር ከ3 ወር እስከ 6 ወር በሰጠው ስልጠና ልጅ የያዙ ሴቶች እና 49 ወንዶችን አስመርቆ ስራ ማስጀመሩን እና ማቋቋሙን በስራ ላይ መሰማራታቸውን ሰምተናል።
በ2ተኛው ዙር እንደ አበባ በጎዳና ላይ የነበሩ ልጆች የያዙ እናቶች እና ወጣቶች በማካተት በወንዶች እና በሴቶች መጠለያ ውስጥ በማስጠለል ሁሉን አቀፍ የሙያ እና የስነልቦና ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ ባሳለፍው ቅዳሜ የምርቃት እና የስራ መስጀመሪያ ፕሮግራም አሰናድቷል።
የተስፋ ለህጻናት ድርጅት ሥራአስኪያጅ አቶ ዘላለም ማሙዬ ለሀገሬ ቲቪ ሲናገሩ
“በሁለተኛው ዙር ስልጠናችን 104 ልጆች የያዙ እናቶች እና ወጣቶችን አካተን አስመርቀናል ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ማሰማራት እንገባለን።” ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ከሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ሚኒስትር፣የአዲስ አበባ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ እንዲሁም የፋይናንስ ቢሮ ድጋፍ ታክሎበት የሚተገበር ሲሆን በተጨማሪም የምስኪያዙናን መድኃኒዓለም ገዳም እና የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ሰምተናል።
የገዳሙ የስብከተ ወንጌል ኅላፊ መልዐከ ብርሃን አባ ጴጥሮስ ሰለሞን(ዶ/ር) በምርቃት ስነስርአቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕት ለዜጎች ተስፋ መሆን በዓለማዊም በመንፈሳዊ ቱሩፋቶች አሉት። ከዚህ ቀደም እንደምናደርገው ይህንን ለመደገፍ አሁንም ዝግጁ ነን ብለዋል። አበባ ስልጠናውን መሰልጠኖ ለሷ ልዩ አጋጣሚ መሆኑን ታነሳለች በተጨማሪም ወደ ፊት የሰው እጅ ከማየት እንደሚታደጋት በማመን።
“እኔ የሰለጠንኩት በንግድ ዘርፍ ነው። የተሳካ ነጋዴ ሆኜ እንኔም ልጄንም ከችግር ማውጣት ነው ምኞቴ።” ብላለች
ስልጠናው ዛሬን ብቻ ሳይሆን እነዚህ ደጋፊ የሌላቸው ዜጎች ነገን ራሳቸውን እንዲችሉ ብሎም ለሀገር እንዲጠቅሙ ማስቻል ዋነኛ ዓላማው አድርጓል።
በመንግሥት ደረጃ ከዚህ ቀደም የጎዳና ተዳዳሪዎችን በማንሳት ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ ለማስገባት ስራ ቢጀመርም የክትትል መላላት እና በሌሎች ምክንያቶች ውጤታማ እንዳልሆነ ሲገለጽ ቆይቷል አሁንም ይህ ግብረሰናይ ድርጅት አሰልጥኖ ማስወጣቱ ብቻ ምን ያህል ውጤታማ ያደርገዋል ምንስ ለውጥ ያመጣል ስንል ጠይቀናል።
አቶ ዘላለም ሲመልሱ ”ከሰለጠኑ በኋላ ዝም ብለን አንበትናቸውም የ3 ወር የቤት ኪራይ፣ቀለብ እና አልባሳትን አሟልተን፤ ከዚህ በተጨማሪ በሰለጠኑት ዘርፍ ለስራ የሚያስፈልጋቸውን በማቋቋም ክትትል እናደርጋለን።”
ብለዋልድርጀቱ ከዚህ ስራ በተጨማሪ ወላጅ የሌላቸው እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ልጆችን ድጋፍ በማድረግ እንደሚያስተምር እና እንደሚያሳድግ ሰምተናል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-16
