ባለፉት ስድስት ወራት ከ8 ሺ በላይ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ይህ የተናገሩት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደርጉበት ወቅት ነበር።
ፓርቲው ከ8 ሺ በላይ የሚሆኑ አባላቱ ላይ የእስር፣ የመባረር እና ከደረጃ ማውረድ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል።
ከፓርቲው አባልነት የተነሱ ግለሰቦች ተገቢ ባልሆነ፣ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በወንድማገኝ አበበ
2024-04-03
