
ኬኒያ ከሶማሊያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር እንደማትከፍት አስታወቀች።
እንደ ኬኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ኃላፊ፤ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ቶር ሶማሊያን ለቆ መውጣት መጀመሩን ተከትሎ ደህንነታችን አደጋ ላይ ነው ብለዋል።
በዚህም ሳቢያ ከ8 መቶ ኪሎሚትሮች በላይ ከሶማሊ ጋር ድንበር የምትጋራው ኬኒያ ደህንነቴን ጠበቅ ማድረግ ይገባኝል ድንበሬን ክፍት ማድረግ አልችልም ብላለች።
ኬኒያ በሶማሊያ ተሸሽጎ የሚገኘው አልሸባብ ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ድንበሯን ሙሉ ለሙሉ ዝግ አድርጋ ትገኛለች።
በሳምሶን ገድሉ
2024-04-03