የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለገጠመው የበጀት እጥረት ፖለቲካዊ ውሳኔ ይሰጠኝ አለ።
ዩኒቨርሲቲው ከመንግሥት የተለቀቀለት በጀት ለሚያደርገው የጥናትና ምርምር ስራ በቂ አለመሆኑን ጠቁሟል።
በበጀት እጥረት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት እየተሳነው መሆኑንም ጠቁሟል።
ተቋሙ ይህን የገለፀው የኅዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው።
ተቋሙ በበጀት እጥረት ሳቢያ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል አደጋ ላይ መውደቁን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው የበጀት እጥረቱ እንዲፈታ ለሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ጥያቄ ቢያቀረብም ምላሽ አለመገኘቱን የጠቆሙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሐጎስ ጥያቄው ፖለቲካዊ ውሳኔን የሚጠይቅ መሆኑ ገልጸዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2024-04-18
