ሀገሬ ቲቪ

ጃኮብ ዙማ ዳግም ወደ ምርጫ ሊመጡ ነው

የደቡብ አፍሪካው የቀድሞው ፕሬዝዳንትና በሙስና ቅሌት ወህኒ ወርደው የነበሩት ጃኮብ ዙማ ሌላ ፓርቲ አቋቁመው በ7ኛው የሀገሪቱ ምርጫ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

የ82 ዓመቱ አዛውንት ዙማ ወደ ስልጣን የሚመጡት ከኔልሶን ማንዴላ ወደስልጣን መምጣት ጀምሮ በመሪነት የነበረውንና እርሳቸውም ያገለገሉትና አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስን በመገዳደር ነው።

ከፈረንጆቹ 1994 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያለው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረሥ በመጪው ምርጫ የዙማን መወዳደር ተከትሎ ሊያሸንፍ እንደሚችሉ ትንበያዎች ያሳያሉ።

ዙማ ድል ቀንቷቸው ወደስልጣን ቢመጡ የቀድሞ አጋሮቻቸውን ሊበቀሉ ይችላሉ የሚል ስጋትም እንዳለ ተነግሯል።

በአስናቀ ማናዬ
2024-04-18