ኬንያ ለ3 ቀናት የሚቆይ የሀዘን ቀን አውጃለች።
ሀገሪቱ አእዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በሄሊኮፕተር አደጋ የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥን ጨምሮ 9 የኬንያ ጦር አባላት መሞታውን ተከትሎ ነው።
የሀዘን ቀን አዋጁ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር ሲሆን ለ3 ቀናት የሚቆይ መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ “በተከሰተውን አደጋ እና የመከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ህይወታቸው ማፉን ስገልጽ በትላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ነው” ብለዋል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-04-19