የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ እና ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ተወያየ።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
አለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን በሙሉ አቅም ለመተግበር ከማስቻል አኳያ በቀጣይ መደገፍ እና አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች መምከራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር በማህበራዊ ገፁ አስፍሯል።
ሁለቱም ተቋማት ኢትዮጵያ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ለመቅረፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም ሁለተኛ ምዕራፍ ሀገር አቀፍ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አድንቀዋል ተብሏል።
በማህሌት አማረ
2024-04-19