ሶማሊያ የቀድሞ መሪዋን ሀሰን ሼክ መሀሙድ ፕሪዝዳንት አርጋ መርጣለች።
ከ 2017 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙት የወቅቱ ፕሬዝዳንት መሀመድ አቡዳላሂ ፋርማጆ በምርጫው ተሸንፈው ለሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ብቻ ክፍት የሆነው የመጨረሻ ድምጽ አሰጣጥ ሀሰን ሼክ መሀመድን የሶማልያ ፕሬዝጋንት አርጎ ሾሟቸዋል። አዲሱ ተሿሚም ለ ቀጣዮቹ አራት አመታት በስልጣን ላይ ይቆያል።
በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2012 እስከ 2017 በፋርማጆ ከመሸነፋቸው በፊት ሼክ መሀሙድ ሶማሊያን ለ 5 አመታት መርተዋል።
ለአመታት ሰላም የራቃት ሶማሊያ ትላንት ይሄን ምርጫ እያኪያሄደች ባለበት ሰዐት በከተማዋ በርካታ የ ፍንዳታ ድምጾች ተሰምተዋል።
የትናንቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትና ሦስት ዙር ድረስ የሄደ ሲሆን ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና የጸጥታ ጉዳይ ምርጫው መደረግ ከነበረበት በ15 ወራት ዘግይቶ እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል።
ይህ ምርጫም በሀገሪቱ ባለው አለመረጋጋት ከሌሎች ሀገሮች የአመራረጥ ሂደት በተለየ መልኩ በ328 የፓርላማ አባላት ብቻ የተከናወነ ሲሆን ከመካከላቸው አንድ የምክር ቤቱ አባል ድምጽ አልሰጡም። በምርጫው ማሸነፋቸው የታወጀው መሀሙድ 214 ድምፅ ሲያገኙ ፋርማጆ 110 ድምፅ በማግኘት በ 104 ድምጽ ከተቀናቃኛቸው ዝቅ ብለዋል።
በ አዲሱ ፕሬዝዳት ድል በከተማዋ የሚገኙ ደጋፊዎች ደስታቸውን በመግለጽ ያመሹ ሲሆን ከተማዋም ብዙ የ ደስታ ተኩሶችን አስተናግዳለች።ታዲያ ለቀጣዮቹ አራት አመታት ሀገሪትዋን የተረከቡት አዲሱ ተመራጭ የተረከቧት ሀገር ቀጣዩ ጉዝዋቸውን የሚፈትን ብዙ መዘዝችን ይዛለች።
3.5 ሚሊዮን ሶማሊያውያን ለከፋ የረሃብ አደጋ እንዲጋረጡ ያደረገውን የድርቅ ተፅእኖ መቋቋም የመንግስታቸው ዋነኛ ፈተና ሲሆን ሌላኛው የአልሸባብ ቡድን ሰፊውን የሀገሪቱን ክፍል መቆጣጠሩን እንደቀጠለ ይገኛል።
በሞቃዲሾ እና በሌሎችም ቦታዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈፀመ ነው። ታዲያ የሶማሊያን ግዛት ከአልሸባብ እጅ መንጠቅ ሌላኛው አቅማቸውን የሚፈትሽ ነገር ነው የ አዲሱን የሶማሊያ ፕሪዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-05-16
