
ከ12 የሚበልጡ የእርዳታ ምግብ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከቻድ ወደ ዳርፉር ሱዳን መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ገልጿል፡፡
በምዕራብ ዳርፉር ከረኔክ አካባቢ በረሃብ ስጋት ውስጥ ለሚገኙ ከ13 ሺ በላይ ሰዎች ተደራሽ የሚሆን ገብስ፣ ዘይት እና ሩዝ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ናቸው ወደ ሱዳን የገቡት፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ ማሰባሰብ እንደሚገባም ተቋሙ አሳስቧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ከዚህ ቀደም በታሪክ አስከፊው የረሃብ ቀውስ በሱዳን መከሰቱን መግለጹ አይዘነጋም፡፡
በሙሴ ከበደ
2024-08-22