ሀገሬ ቲቪ

"ሸኔ" ከአልሸባብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው

መንግስት ሸኔ ሲል የሚጠራው እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ነኝ የሚለው ቡድን ከአልሸባብ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዳለው የኬንያ የመረጃና ደህንነት ኃላፊዎች ገለፁ።

ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ እና የኬንያ የመረጃ ተቋማት በአዲስ አበባ ውይይት ባደርጉበት ወቅት ነው።

የኬንያ ድህንነት ተቋም በቅርቡ ሰሜናዊ ኬንያ ውስጥ ሁለት የኮሪያ ዜጎችን በማገት ለአልሸባብ አሳልፎ እንደሰጠ ተናግረዋል።

በተለይ በኬንያው ሞያሌ አካባቢ ከኢትዮጵያ የሚነሱ ታጣቂዎች በሲቪሎችና በፀጥታ አካላት ላይ ጥቃት እየፈፀሙ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ቡድኑ በድንበር አካባቢ በኮንትሮባንድ፣ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ በሕገ-ወጥ ማዕድን ማውጣት ድርጊቶች ተሠማርቷል መባሉን የኢትዮጵያን ፕሬስ ድርጀት ዘግቧል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከቡድኑ በጉዳዩ ላይ የተባለ ነገር የለም።

በማህሌት አማረ
2024-08-22