ሀገሬ ቲቪ

“በኢትዮጵያ እስካሁን በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተያዘ ሰው የለም” ጤና ሚኒስቴር

ጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እስካሁን በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተያዘ ሰው እንደሌለ አስታወቀ።

በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ የሚገኘው በሽታው እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ አልገባም ያለው ሚኒስቴሩ፤ በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ካሉባቸው ሀገራት የሚመጡ ሰዎችን በሚመለከት በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የልየታና የጥንቃቄ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በሽታው ስጋት መሆኑን ካወጀበት የፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት የጤና ሚንስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ አሁንም ቢሆን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በምንገናኝባቸው ስምንት የድንበር አካባቢዎች የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለዋል።

ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ትምህርት በመውሰድ ክትባት ከሚያመርቱ ሀገራት ጋር ንግግር መጀመሩም ተነግሯል።

በበላይሁን ፍሰሃ
2024-08-22