ሀገሬ ቲቪ

ብሔራዊ የአየር ማረፊያ የዱር እንስሳት ኮሚቴ ተቋቋመ።

የአዕዋፋት እና የአውሮፕን ግጭት አደጋን በቋሚነት ለመከላከል ያለመ ብሔራዊ የአየር ማረፊያ የዱር እንሰሳት ኮሚቴ መቋቋሙ ተነገረ።

የኮሚቴው መቋቋም አላማ የአዕዋፋትና የእንሰሳት ከአውሮፕላን ጋር ግጭት አደጋ የሚያጋጥመውን በቋሚነት ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።

ህገ- ወጥ የከብት እርድ፣ ወደ አካባቢው የሚለቀቁ ደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻዎች፣ የቁም ከብት ገበያ እና ሌሎችም ምክንያቶች አዕዋፋት የአየር ማረፊያ አካባቢ እንዲያዘወትሩ ምክንያት ናቸው ተብለው ተቀምጠዋል።

ይህ የተነገረው በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ አወያይነት የወፎችና የአውሮፕን ግጭት አደጋን ለመከላከለ ያለመ ምክክር በተደረገበት መድረክ ላይ መሆኑን ከትራንስፖርትና ሎጂስትቲክስ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-08-22