
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ የአስተዳደር መቀመጫ የሆነውን የሰገን ከተማን ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ተቆጣጥረው የነበሩ ታጣቂዎች አካባቢውን ለቀው መውጣቸው ተነግሯል፡፡
ነዋሪዎች ነገሩኝ ብሎ የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው፤ ታጣቂዎቹ ትናንት ከተማውን ለቀው የወጡት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ከተማው መግባታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።
አሁን ሠራዊቱ በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ አንጻራዊ መረጋጋት እየመጣ ነው ተብሏል፡፡
በ23 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላይ ሰፊ የንብረት ዝርፊያና ውድመት በመፈጸም ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባ የገለጹ ሲሆን ታጣቂ ኃይሉ በ8 ፖሊስ አባላትና 5 ሲቪል ነዋሪዎች ላይ የግድያ ተግባር መፈጸሙን አንስተዋል፡፡
በወንድማገኝ አበበ
2024-08-23