በኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የሚሳተፉ ኮንትራክተሮች የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያውን ተከትሎ የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
ተቋሙ የሚያከናውናቸው አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች በውጭ ኮንትራክተሮች የሚገነቡ በመሆናቸው ጥያቄው ከሁሉም የሚመጣ ነው ብሏል።
ጭማሪው የሚጠበቅ ቢሆንም መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ለመግለፅ ጊዜው ገና መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ጠቁመዋል፡፡
ከኮንትራክተሮቹ ጋር ውል ሲፈረም የዋጋ ለውጥ የሚያስከትል ክስተት ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት ቀድሞም መኖሩንም አስረድተዋል።
ከኮንትራት ውል በተጨማሪ ተቋሙ የወሰዳቸው ብድሮች የዶላር መሆናቸው አመላለሱ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ጠቁመዋል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
በይስሃቅ አበበ
2024-08-26