የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ትናንት እሁድ ከ300 በላይ የሆኑ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል መተኮሱ ተነገረ።
እስራኤልም ሮኬቶችን ለማክሸፍና የመልስ ምት ለመስጠት ጄቶችን መጠቀሟ የተነገረ ሲሆን፤ አንድ ተዋጊዋ እንደተገደለባትም አስታውቃለች።
በሄዝቦላህ በኩልም 3 ተዋጊዎች መገደላቸው ተነግሯል።
በኢራን ይደገፋል በሚል የሚጠቀሰው ሄዝቦላህ፤ የትናንቱ ጥቃት ከቀናት በፊት ለተገደሉበት አመራሩ መልስ የሰጠበት መሆኑን አስታውቋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ቀጣይ እርምጃዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
በእሱባለሁ ጋሻው
2024-08-26
